Monday, September 21, 2015

Dear Family (ለውድ የሥጋ ቤተሰቦቼ)





"Birch Wheel" by Jo Thilwind 


Dear Family, 

I never thought I’d feel the need to write you. I used to pretend that it didn’t bother me to not know you, but it does. I felt like I would betray my adoptive family. I also never thought it was possible to even find you because for some reason, I don’t even know your names or the circumstances around my birth. Are you aware of this? Granted, I was born at a tumultuous time in 1985. I can only imagine what you were going through. All I know is that I feel awful between the months of September and November, which is probably around the time of my birth. I feel like my body remembers something that my mind cannot. 

I’ve tried searching for you but it’s very difficult because you or the person you left me with did not document your full names. I’m not sure if my last name belongs to my mother or my father. I’m still waiting to hear back from a searcher, we will see. I’m not sure what it will take to find you. I don’t even know if you want to be found since I don’t know if you abandoned me intentionally or not. I feel like there are a lot of lies and secrecy around my relinquishment. It’s hard to find people involved in my adoption process and the ones I do know insist that they told me all they know. 

Anyway, the truth is that searching has become a business and I don’t have enough money to pay for a full-fledged search. I’ve been approached by journalists who want to help find you but I’ve declined their offers. I don’t want anyone putting words on my experience or yours, especially not without your consent and full approval. I also don’t want anyone making money or getting a book deal by writing about us. I’ve had so little control in what has happened to me. Having someone else profit from this is just another form of control and exploitation. I refuse, so I’m choosing the long route, which is to gather information bit by bit.

To be honest, I’m scared to return to Ethiopia a second time. I don’t want to go there and come back empty-handed. You could be living in one of the many remote villages that are quite inaccessible for non-natives and non-Amharic speakers. Maybe you’re in Addis or maybe you’ve even left the country. Anything is possible, but I’d be surprised if you are in the same place though, because I was told you were internally displaced since you were fleeing the famine.

I guess the other thing is that, I’m scared to uncover some awful truth about you. I’m even more scared that I won’t be able to handle it. I know our story is tragic. When I returned to Ethiopia the first time in 2009, I felt it. It was a very heavy feeling that I can’t express in words. I mourned for a few days before we headed North to Gondar. I did not look for you. I was hurt and did not understand why you left me. I’m sure you have a thousand good reasons, but my inner child does not care about them. She just feels hurt. 

I don’t blame you for what you did, whatever you did. We’re all just trying to survive. We don’t always make the best decisions or we think we have but our judgement was clouded at the time by our circumstances. I cannot say that I’m at peace with what happened or with your decision. I’m still very angry, not at you because I don’t know what you did, but at the situation and how it was played out.

I’ve been trying to accept the injustice of not knowing you and not being able to find you but I’ve been unsuccessful. I can’t get over wrongdoings easily, especially if they aren’t explained. It’s like a big lump in my throat that I can’t swallow. I’ve tried to redirect my angry energy towards motivating other adoptees to speak out and doing lots of physical activity. It helps to a certain extent.

In the meantime, I will try to be patient about looking for you. I’m writing you this letter and making it public because I need to release this anger and sadness into the universe (sorry, not sorry). I also want you to know that I am thinking about you even if I really don’t like talking about it publicly.

I know I’m not the only one who feels like this. As I write, I’m also thinking of the thousands and thousands of adoptees and birth parents in my situation. I share their pain and their struggles. I’m sure you do too. I hope you have found healthy ways to release whatever your feelings have about our situation. I will try to respect your thoughts and feelings if we ever meet. I hope we do. But if we don’t, I’ll always know that I’m connected to you because I feel it deeply. I know that SO much of me comes from you. You are a big part of me even if you’re not in my life. And I am also part of you even if I am missing from your lives. 

I will leave you with the words of E. E Cummings which sums up a little how I feel about losing you, my unknown family but still being close to you; “I carry your heart with me (I carry it in my heart), I am never without it (anywhere I go, my dear; and whatever is done by only me is your doing, my darling).

I wish you well,

Kassaye 



ለውድ የሥጋ ቤተሰቦቼ፣

ለእናንተ ለመጻፍ እነሳሳለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር። እናንተን ማወቅ ያን ያህል ግድ እንደማይሰጠኝ አስመስል ነበር፤ ግን ያሳስበኛል። በማደጎ ያሳደጉኝን ቤተሰቦቼን እንደመካድ ይሆንብኛል ብዬ አስብ ነበር። እናንተን ማግኘትም የሚቻል ነገር ነው ብዬ አስቤ አላውቅም፤ ምክንያቱም ስማችሁንም ሆነ ስወለድ ስለነበረው ሁኔታ ምንም የማውቀው ነገር የለም። ስለዚህ ነገር ታውቃላችሁ? የማውቀው ነገር፥ እጅግ ዘግናኝ በሆነው ጊዜ በ1977 መወለዴን ነው። በምን አይነት አስቸጋሪ ወቅት እያለፋችሁ እንደነበር በሃሳቤ ልስለው ብቻ ነው የምችለው። የማውቀው ነገር ቢኖር ከመስከረም እስከ ህዳር ባሉት ቀናት ጭንቅ ጥብብ ይለኛል። ይህም ምናልባት በዚህ ወቅት ስለተወለድኩ ይሆናል የሚል ግምት እንድይዝ አድርጎኛል። አእምሮዬ ጓዳ ላይ ያልተከተበ ግን በልቦናዬ የተቀረጸ አንዳች ትዝታ ወደ ሰውነቴ እየመጣ እንደሆነ እንዳስብ ያደርገኛል።

እናንተን ለመፈለግ ሞክሪያለሁ። ነገር ግን እናንተ ወይም እኔን ያስረከባችሁት ሰውዬ ሙሉ ስማችሁን ስላልመዘገበው ድካሜ ሁሉ በጣም አስቸጋሪ ሆኗል። ከስሜ ቀጥሎ ያለው ስም የእናቴ ይሁን የአባቴ እንኳን እርግጠኛ አይደለሁም። እናንተን እንዲያስስ አደራ ካልኩት ሰው ምላሽ እየተጠባበኩኝ ነው። የሚሆነውን እስኪ እናያለን። እናንተን ለማግኘት ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስፈልገኝ እርግጠኛ አይደለሁም። ፈልጌ እንዳገኛችሁ ትፈልጉ እንደሆን እንኳ አላውቅም። ምክንያቱም እኔን የተዋችሁኝ ሆነ ብላችሁ ይሁን ወይም ከአቅም በላይ በሆነ ችግር አላውቅም። በእኔ የቤተሰብ ቅይይር ዙሪያ በርካታ ውሸቶችና ሚስጥሮች እንዳሉ ይሰማኛል። በማደጎ በመሰጠቴ ሂደት የተሳተፉ ሰዎችን ማግኘት በጣም ከባድ ነው። የማውቃቸው ውስን ሰዎችም የሚያውቁትን በሙሉ እንደነገሩኝ አበክረው ይነግሩኛል።

ለማንኛውም፥ እውነቱ ፍለጋ ሥራዬ መሆኑና ለተሟላ የፍለጋ ስራ ግን በቂ ገንዘብ የሌለኝ መሆኑ ነው። የተለያዩ ጋዜጠኞች ቀርበው እናንተን ለመፈለግ በማደርገው ጥረት ሊያግዙኝ እንደሚፈልጉ ገልጸውልኛል። እኔ ግን ችሮታቸውን ችላ ብዬዋለሁ። በእኔ ወይም በእናንተ የህይወት ጉዞ ላይ ማንም ቃላትን እንዲሰድር አልፈልግም። በተለይ በእናንተ ላይ፤ ቢያንስ ይሁንታችሁን ሳትሰጡትና ሙሉ በሙሉ ሳትፈቅዱ ማንም ምንም እንዲል አልሻም። ማንም ሰው ስለእኛ ጉዳይ በመፃፉ ምክንያት ገንዘብ እንዲያገኝ ወይም የመጽሃፍ ህትመት ውል እንዲገባ አልፈልግም። በእኔ ላይ ስለሆነው ነገር የነበረኝ የቁጥጥር አቅም በጣም ኢምንት ነው። በዚህ እድለ ቢስነት ሌላ ሰው ትርፍ እንዲያጋብስበት መፍቀድ ለሌላ አይነት ቁጥጥር መውደቅ ወይም ራስን ለብዝበዛ አሳልፎ መስጠት ነው። እምቢ አልኩኝ፣ እናም ረጅሙን መንገድ መረጥኩኝ፤ ወደ እናንተ የሚያደርሱኝን መረጃዎችን አንድ በአንድ መልቀም።

እውነቱን ለመናገር፣ ወደ ኢትዮጵያ ዳግም ለመመለስ በጣም እፈራለሁ። ወደ’ዛ ሄጄ እንደገና ባዶ እጄን መመለስ አልፈልግም። ምናልባት በጣም ሩቅ ከሆኑትና ለአገሬውና አማርኛን አጥርቶ ለሚናገረው ካልሆነ በስተቀር ለማንም ተደራሽ ካልሆኑት የገጠር መንደሮች በአንዱ እየኖራችሁ ሊሆን ይችላል። ምናልባት በአዲስ አበባ እየኖራችሁ ሊሆን ይችላል ወይም ከነአካቴው እናንተም ከአገር ወጥታችሁ ሊሆን ይችላል። ማንኛውም ነገር ተከስቶ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አሁንም ያኔ በነበራችሁበት ቦታ ከሆናችሁ በጣም ይገርመኛል። ምክንያቱም ከርሃቡ ሽሽት ከቀያችሁ ሙሉ ለሙሉ ተፈናቅላችሁ እንደነበር ተነግሮኛል።

ሌላው ነገር ደግሞ ስለእናንተ መጥፎ ነገር አውቅ ይሆን የሚል ስጋት የያዘኝ ይመስለኛል። የማውቀውን ነገር ችዬ መሸከም ያቅተኛል የሚለው ፍራቻም የበለጠ ያሳስበኛል። ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ በመጣሁበት 2001* ዓ/ም ይህ ነገር በደንብ ተሰምቶኛል። የተሰማኝ ስሜት በቃላት ልገልጸው የማልችለው ከባድ ስሜት ነበር። የሰሜኑን አቅጣጫ ይዘን ወደ ጎንደር እስክንጓዝ ድረስ ለተወሰኑ ቀናት በሃዘን ስሜት ተውጫለሁ። በእርግጥ እናንተን አልፈለኩም ነበር። ውስጤ በጣም ተጎድቷል። እንዴት ትታችሁኝ ልትሄዱ እንዳስቻላችሁ ሊገባኝ አልቻለም። እርግጠኛ ነኝ ለዚያ ውሳኔያችሁ አንድ ሺህ ጥሩ ምክንያቶች ሊኖራችሁ ይችላል። ውስጤ ያለው ስሜት ግን ስለሰበቦቻችሁ ግድ አይሰጠውም። ለውስጤ የሚተርፈው መጎዳት ብቻ ነው።

ምንም አደረጋችሁ ምን፣ ስላደረጋችሁት ነገር በጭራሽ አልወቅሳችሁም። ሁላችንም የምናደርገው ሕይወትን የማትረፍ ጥረት ነው። ሁልጊዜም ትክክለኛውንና ምርጡን ውሳኔ አንወስንም። ወይም ምርጡን ውሳኔ የወሰንን ቢመስለንም፣ እውነታው ግን ብያኔያችን በጊዜው በነበርንበት ሁኔታ እንደ ጭጋግ የከለለው ሊሆን ይችላል። የሆነው ነገር ወይም የወሰናችሁት ውሳኔ ሰላም ሰጥቶኛል ማለት አልችልም። አሁንም ድረስ ውስጤ ብግን እንዳለ ነው። ግን በእናንተ አይደለም፣ ምክንያቱም ምን እንዳደረጋችሁ እንኳ በውል ስለማላውቅ። በሁኔታውና ሁኔታው ባለፈበት መንገድ ግን ውስጤ ተጎድቷል።

እናንተን ያለማወቅና ፈልጎ ያለማግኘትን ኢ-ፍትሃዊ ያልሆነ መንገድ ለመቀበል ብዙ ጥሬያለሁ። ግን ምንም ሊሳካልኝ አልቻለም። ስህተቶችን በቀላሉ መርሳታና ማለፍ አልችልም፤ በተለይ አስፈላጊው ማብራሪያ ሳይቀርብልኝ ሲቀር። ጉሮሮዬ ላይ ተሰንቅሮ አልወርድልኝ እንዳለ አንዳች ነገር ሆኖብኛል። ብስጭቴን ሌሎች የማደጎ ልጆችም እንዲናገሩ ወደ ማነሳሳትና በርካታ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ወደ መስራት አዙሬዋለሁ። ይህም በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ረድቶኛል።

ለጊዜው፣ እናንተን ለማግኘት ባለኝ ጉጉት ላይ ትዕግስተኛ ለመሆን እሞክራለሁ። ይህን ደብዳቤ የምጽፍላችሁና ጉዳዬን ለአደባባይ የማበቃው ይህን ብስጭቴንና መከፋቴን ወደ ዓለም ማውጣት ስላለብኝ ነው። (ይቅርታ። ኧረ እንደውም የምን ይቅርታ ነው?) ደግሞም በአደባባይ ስለጉዳዩ ማውራት ባልፈልግ እንኳ ስለእናንተ ግን ሁኔም እንደማስብ እንድታውቁልኝ እፈልጋለሁ።

እንዲህ አይነት ስሜት የሚሰማው እኔን ብቻ እንዳልሆነ አውቃለሁ። ይህን እየጻፍኩኝም ቢሆን፣ በሺዎች ስለሚቆጠሩት የማደጎ ልጆችና ስለየስጋ ወላጆቻቸው ሁኔታ እያሰብኩኝ ነው። ህመማቸውን እና ትግላቸውን እጋራለሁ። እናንተም እንደምትጋሯቸው እርግጠኛ ነኝ። ስለሁኔታችን የሚሰማችሁን ማንኛውንም አይነት ስሜት ለማስተንፈስ የሚያስችላችሁ ጤነኛ የሆኑ መንገዶች አጊኝታችኋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ምናልባት ከተገናኘን፣ ሃሳባችሁንና ስሜታችሁን በሙሉ ለማክበር እሞክራለሁ። እንደምንገናኝ ተስፋ አደርጋለሁ። ነገር ግን ካልተሳካልን፣ ምንጊዜም ቢሆን ከእናንተ ጋር ቁርኝት እንዳለኝ አውቃለሁ። ምክንያቱም ውስጤ ድረስ ዘልቆ የሚሰማኝ ስሜት ስለሆነ። አብዛኛው እኔነቴ ከእናንተ እንደመጣ አውቃለሁ። በሕይወቴ ውስጥ ባትኖሩም እንኳ፣ የእኔ ትልቁ ክፋይ ናችሁ። እንዲሁም ምንም እንኳ ከሕይወታችሁ ብጎድልም፣ እኔም የእናንተ አንድ አካል ነኝ። ስለዚህ፣ እናንተን፣ የማላውቃችሁን ግን ደግሞ ቅርቦቼ እንደሆናችሁ የሚሰማኝን ቤተሰቦቼን፣ በማጣቴ የሚሰማኝን ስሜት በተወሰነ መልኩም ቢሆን በሚገልጽልኝ የኢ.ኢ. ከሚንግስ ቃላት እሰናበታችኋለሁ። “ልባችሁን በውስጤ ተሸክሜዋለሁ (በልቤ ውስጥ ይዠዋለሁ)፣ መቼም ቢሆን ተለይቼው አላውቅም (የትም ቦታ ብሄድ፥ የእኔ ውዶች፥ ማንኛውም በእኔ ብቻ የሆነ ነገር በሙሉ የእናንተም ነው፥ ውዶቼ)”። “I carry your heart with me (I carry it in my heart), I am never without it (anywhere I go, my dear; and whatever is done by only me is your doing, my darling).”

መልካሙን ሁሉ እመኝላችኋለሁ። ካሳዬ



Kassaye is an Ethiopian adoptee living in Montréal Québec (Canada). She co-founded Ethiopian Adoptees of the Diaspora and is currently working on an anthology by Ethiopian adoptees entitled "Lions Roaring Far From Home".


Amharic translation by Zecharias Zelalem.

Photo credit: http://www.saatchiart.com/art/Painting-BIRCH-WHEEL/78806/1264750/view